ስለእኔ እጮኛዬ ታለቅስልኛለች ከልቧ ካንጀትዋ ትንሰቀሰቃለች እዳዬን ጓዶቼ ይመልሱልኛል ባለአንጣዎቼ ጽዋዎቻቸውን ያነሱ ይኾናል ስለእኔ ጤንነት ይጐነጬልኛል ምንአልባት ዘፈንም ይዘፈንልኛል። መንፈስ አርኪ መጽሐፍት በቃ እኔ አላነብብም ተወዳጅ ጊታሬም ጅማቶች የሏትም የአለም በቃኝ ውስጥ ነኝ አይታየኝ ሰማይ አላይ መሬትንም አላይም ፀሐይን ጨረቃን እንዲሁም። ነፃነት ለማየት የለኝም እኔ መብት ተወስኖብኛል ግድግዶች መመልከት መዞር ወደ ግራ ወደ ቀኝም ክልክል ከቀናኝ ሰማዩን በህልም አይ ይኾናል። ከውጭየ ተዘጋብኝ የቁልፍ ጋን ተሰብሮ ከእስራት ስፈታ ሰብእና ተከብሮ ጊታሬም ተሰጥታኝ እንደገና ስቃኝ ወዳጆች ጓዶቼ ሲያቅፉኝ ሲስሙኝ በአል ሲያዘጋጁ እኔን ሊቀበሉኝ ለካስ ነው ተኝቼ በህልሜ የአየኹኝ።
© Nigusie Kassaye W. Michael. Translation, 2014
© Nigusie Kassaye W. Michael. Performance, 2014