አንተን ባልንጀራህ ተአማኝነቱ ከአጠራጠረህ ወይ ወዳጅ ወይ ጠላት መኾኑን ካላወቅህ ውሰደው ቀጥ ብሎ ከቆመ ተራራ አደጋን ሳትፈራ አትተወው ከመኻል መንገድ ላይ እሰርና ምራው ወገቡን ከአንተ ወገብ ላይ እና ትረዳለህ መኾኑን ሀቀኛ ወይ መልቲ አታላይ። ስትወጡ ተራራ በድንገት አዳልጦት ድንጋጤ ገብቶት ከራደ በፍርሃት አይደለም መንፈሰ ጠንካራ ለአንተ እሱ አይኾንም ፍጹም ባልንጀራ ግን እንዳትወቅሰው ዝም በልና ተወው እወቀው ከእንደዚህ አይነቱ ወዳጅ ጋር አይወጡም ወደ ላይ ግጥሞችን አይገጥሙም ስለእሱ ዘፈንም አይዘፍኑም እንደኾነ አጋር ስለዚህ ከእሱ ጋ ተለያይ። ግን ካላለቀሰ እንባውን ካልረጨ ካልተነጫነጨ ፊቱ ተኮሳትሮ ግንባሩ ተቋጥሮ በንዴት ውስጥ አንጀቱ አርሮ ሲሄድ ተከትሎህ በድንገት ሳታስብ አለቱ አሟልጮህ ብትወድቅ እድሉን እየተሳደበ ዕለቱን እየተራገመ ከያዘህ ድጋፉን ከሰጠህ አንተን ተከትሎ ደርሶ ከቁንጮው ላይ ከቆመ በኩራት እመነው እንደራስህ አድርገህ በእሱ ላይ ተመካ ይብቃ ጥርጣሬህ።
© Nigusie Kassaye W. Michael. Translation, 2014
© Nigusie Kassaye W. Michael. Performance, 2014