በወርቃዋማዊቷ አፍሪካ መሀል እምብርቷ ላይ ሳይታሰብ ሳይታወቅ ዱብ አለ ዕዳ ከላይ መጥለቅለቅ እንደገና ድንገት ይመጣልና ብሎ አንድ ቀጭኔ ከሜዳ ፍየሊት ጋር አሉ ፍቅር ጀመረ ሲል ዜና ያበሰረ አቶ ዝሆን ነበረ። ይኽን ወሬ የሰሙት ተረበሹ መንጋ አራዊት ጀመሩ ጩኸት ፉጨት።   ግን አሮጌ በቀቀር ቅርንጫፎች ላይ የሚኖር አለ ጮክ ብሎ እስከማውቀው እኔ ኹሉም ይታየዋል ረዥም ነው ቀጭኔ። እንዲህ ሲል ተናገረ ያፈቀረው ቀጭኔ አዎን ቀንዳማ ነች የወደድኳት ፍየል ተቃራኒ አለ? መኾኑን ኹሉም እኩል ዘመድ አዝማዶቼ ተቃውሞ ካነሱ ልብ አድርጉ እለያለሁ እኔ ከእነሱ። ተረበሸ መንጋ አራዊት ተጀመረ ጩኸት ፉጨት።     በቀቀሩ አሮጌው ቅርንጫፎች ላይ ኗሪው አለ ጮክ ብሎ ረዥም ነው ቀጭኔ ኹሉም የሚታየው ይመስለኛል እኔ። ለፍየሊቷ አባት ያስፈልጋል በእውነት? እንዲህ ዓይነቱ አማት ግንባሩን አሉት ወይ አናቱን ስለሌለው ልዩነት። የቀጭኔዎቹ ልጅ ባል አልነበረም ጅላጅል ሚስቱን ይዞ ተለየ ከአባት ከእናቱ መንደር ያለሀሳብ ለመኖር ገባ ከጎሾች ሰፈር። በወርቃዋማዊቷ አፍሪካ መሀል እምብርቷ ላይ ኑሮን የሚያስጠላ መሞትን የሚያስመኝ ሳይታሰብ መጣ የህይወት ገጠመኝ ተጣሰ ልማድ ወግ አይሰራም በፍጹም ህግ ቀጭኔ አባት ቀጭኔ እናት ይረጫሉ የአዞ እንባ ጠልፎ ስለአገባ ልጃቸውን ቆንጂት ወጠምሻ የጎሽ ወጣት መሪሩ ሀዘናቸው አይገለጽ በቃላት። በቀጭኔው ድፍረት ሰዎች አትፍረዱበት ጥፋተኛው እኮ ቀጭኔ ረዥም ነው ኹሉም የሚታየው እያለ የጮኸው ቅርንጫፎች ላይ ኗሪው አሮጌው በቀቀር ነው።
© Nigusie Kassaye W. Michael. Translation, 2014